ለአምራች ኢንዱስትሪ ድጋፍ ሰጭ ባለሙያዎች የ3 ቀናት የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ

ለአምራች ኢንዱስትሪ ድጋፍ ሰጭ ባለሙያዎች የ3 ቀናት የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ አምራች እና አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን አቅም ለማሻሻል እንዲሁም የአገልግሎት ጥራትን በማሳደግ ሀገራዊ እድገትን ማረጋገጥ የሚያስችሉ በርካታ የአቅም ማሻሻያ ስልጠናዎችን በመስጠት ላይ የሚገኝ ሲሆን ይህንኑ ተቋማዊ ጥረት አጠናክሮ በመቀጠል ለአምራች ኢንዱስትሪ ድጋፍ ሰጭ ባለሙያዎች የ3 ቀናት የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጥቷል፡፡

ስልጠናው በገቢ ምርት መተካት፡ ለውጭ ምርት ሴክተሮች የብቃት ድጋፍ በማድረግ ዙሪያ እና በቴክኖሎጂ ፈጠራ እና ዲጅታል አጠቃቀም ላይ ትኩረቱን ያደረገ ሲሆን ከኢትዮ ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ፣ ከድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ፣ ከድሬዳዋ አስተዳደር ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ እንዲሁም ከትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ የተውጣጡ የኢንዱስትሪ ድጋፍ ሰጭ ባለሙያዎች ለ3 ተከታታይ ቀናት ያሳተፈ መሆኑ ታውቋል፡፡

ስልጠናውን በይፋ ያስጀመሩት የድሬዳዋ አስተዳደር ኢንደስትሪና ኢንቨስትመንት ም/ቢሮ ሃላፊ የሆኑት ሼክ ኡስማን እንደተናገሩት ስልጠናው በዩኒቨርስቲውና በአስተዳደሩ በትብብር ሲሰሩ የነበሩ ትልልቅ የአቅም ግንባታ ፕሮጀክቶች አካል ነው ብለዋል፡፡

በስልጠናው ወቅት የኤክስፖርት ምርት የድጋፍ ስልትና መለያ መስፈርቶች፣ የገቢ ምርት የመተካት አቅጣጫና የመተኪያ ስልቶች፣ የቴክኖሎጅና የኢኖቬሽን እንዲሁም ድጅታላይዜሽን አጠቃቀም ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።

ስልጠናውን ለባለሙያዎች የሰጡት የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ መምህር እና ተመራማሪ የሆኑት ዶ/ር ሙሉጌታ ግርማ እንደተናገሩት ከባለሙያዎች ጋር ተገናኝቶ መመካከር በዘርፉ እድገት ላይ የሚስተዋለውን የአቅም ውስንነት ከመቅረፉም ባሻገር ሀገራዊ ፋይዳው የጎላ በመሆኑ እንደ አስተዳደር ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ መሆኑን ዋል፡፡

Recent News