ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ከከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የከተሞች ገቢ ሪፎርም ፕሮጀክት ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ሲሰጥ የቆየው የከተማ ፕላን፣ መሬት እና የከተማ ፋይናነስ ዘርፍ ሥልጠና እና የብቃት ማረጋገጫ ምዘና ፕሮጀክት ማጠቃለያ መርሀግብር ተካሄደ። በስልጠናው ከአፋር፣ ከሶማሌ እና ከሀረሪ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እንዲሁም …
በመልካም ስነ-ምግባር የታነፀና ከሱስ ነፃ የሆነ ሀገር ተረካቢ ትውልድ ለመፍጠር በትኩረት እየሰራ መሆኑን የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ገለጸ። የዩኒቨርሲቲው ማርኬቲንግ ትምህርት ክፍል ለ8ኛ ጊዜ ባካሄደው የማህበረሰብ ንቅናቄ መድረክ ወጣቶችን ከአደንዛዥ ዕፅ ተጠቃሚነት ለመከላከል ታሳቢ ያደረገ እና በርካታ ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ደማቅ መድረክ …
የብዝሃነትና የመቻቻል ተምሳሌት በሆነችው ድሬዳዋ ከተማ የሚገኘው ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ “ብዝሃነት እና የሽግግር ፍትህ ለሀገር ግንባታ እና ዘላቂ ሰላም” በሚል መሪ ቃል ለ5ኛ ጊዜ በድምቀት አካሂዷል። ዩኒቨርሲቲው ብዝሃነትን የተቋሙ መገለጫና እሴት በማድረግ የሚሰራቸውን ስራዎች አጠናክሮ ቀጥሏል። የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም …
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ያመረታቸውን ዘመናዊ የሮኬት ስቶቭ የምግብ ማብሰያ ምድጃዎችን ለድሬዳዋ ግብርና፤ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ያስረከበ ሲሆን ዩኒቨርሲቲው ወደ ተግብር ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ እያደረገ ያለውን ስትራቴጂካዊ ሽግግር ያመላከተ ስራ ሆኗል፡፡ ፕሮጀክቱ ዩኒቨርሲቲው በቋሚነት ከሚሰራቸው የቴክኖሎጂ ሽግግር ስራዎቹ አንዱ ከመሆኑም ባሻገር …
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የተለያዩ የሲሚንቶ ፋብሪካዎችን ያሳተፈ እና ፋብሪካዎች ባሉባቸው ተግዳሮቶች ዙሪያ የሰራውን ጥናት ይፋ ያደረገበት መርሃ ግብር ዛሬ ተካሄደ፡፡ ድሬዳዋ ሲሚንቶን በማምረት ቀዳሚ ከተማ ከመሆኗም በላይ 3 የሲሚንቶ ፋብሪካዎች የሚገኙባት ለዘርፉ እጅግ ተፈላጊ የሆኑ ጥሬ እቃዎች የሚገኙባት ከተማ ናት፡፡ የድሬዳዋ …
በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ የሚወዳደሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ያላቸውን የትምህርት ፖሊሲ አማራጮች ለህዝብ የሚያስተዋውቁበትና እርስ በእርስ የሚከራከሩበት መድረክ በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ተካሄደ። መድረኩን የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ትምህርት ክፍል ያዘጋጀው ሲሆን፣ ዓላማውም ፓርቲዎች ለሀገሪቱ የትምህርት ሥርዓት ያላቸውን ራዕይ መራጩ ማህበረሰብ …







